ወሬ ደግሞም አሉባልታ; ክፉ መናገር ተመልከቱ አንዳንዴም በግማሽ እውነት፣ ህዝብን ከእግዚአብሔር እና ከሁሉም ጥሩ ነገሮች ለማዞር ሰይጣን ወሬን እና ጸብን ያባዛል (ሔለ. ፲፮፥፳፪፤ ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፩)። የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት አንደኛው ምልክት ሰዎች ስለጦርነቶች እና ስለጦርነቶች ወሬ መስማታቸው ነው (ማቴ. ፳፬፥፮፤ ት. እና ቃ. ፵፭፥፳፮፤ ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፳፫)