የጥናት እርዳታዎች
ኢያሱ


ኢያሱ

የብሉይ ኪዳን ነቢይና መሪ፣ እናም የሙሴ ምትክ። የእስራኤል ልጆች ከማምለጣቸው በፊት በግብጽ የተወለደ ነበር (ዘኁል. ፲፬፥፳፮–፴፩)። እርሱና ካሌብ ወደ ከነዓን ከተላኩት ሰላዮች መካከል ነበሩ። ስለምድሩ ጥሩ ሀተታ የሰጡት እነርሱ ብቻ ነበሩ (ዘኁል. ፲፫፥፰፣ ፲፮–፴፫፲፬፥፩–፲)። በ፻፲ አመቱ ሞተ (ኢያ. ፳፬፥፳፱)። ኢያሱ የትሁት ነቢይ-ጀግና ታላቅ ምሳሌ ነበር።

መፅሐፈ ኢያሱ

ይህ መፅሐፍ በኢያሱ ስመ የተጠራው እርሱ ዋናው ተሳታፊ ስለነበረ ነው እንጂ እርሱ ጸሀፊው ስለሆነ አይደለም። ምዕራፍ ፩–፲፪ ስለከነዓን መሸነፍ ይገልጻሉ፤ ምዕራፍ ፲፫–፳፬ የእስራኤል ልጆች ምድሯን እንደተከፋፈሉ እና ስለኢያሱ የመጨረሻ ምክር ይናገራሉ።

በመፅሐፈ ኢያሱ ውስጥ ሁለት ታዋቂ ቁጥሮችም ጌታ እርሱን ቅዱሣት መጻህፍትን እንዲያሰላስል ያዘዘው (ኢያ. ፩፥፰) እና ኢያሱ ህዝቡን ለጌታ ታማኝ እንዲሆኑ የጠራበት ናቸው (ኢያ. ፳፬፥፲፭)።