ጢሞቴዎስ
በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በጳውሎስ አገልግሎት ጊዜ ከጳውሎስ ጋር አብሮ የሚጓዝ ወጣት ሚስዮን (የሐዋ. ፲፮፥፩–፫፤ ፪ ጢሞ. ፩፥፩–፭)፤ አባቱ ግሪክ እናቱ አይሁድ ነበሩ፤ እርሱና ወላጆቹም በልስጥራ ይኖሩ ነበር።
ጳውሎስ ስለጢሞቴዎስ “እንደ እምነት ልጁ” ይናገር ነበር (፩ ጢሞ. ፩፥፪፣ ፲፰፤ ፪ ጢሞ. ፩፥፪)። ጢሞቴዎስ ምናልባት የጳውሎስ በጣም የታመነ እና ችሎታ ያለው ረጂ ነበር (ፊልጵ. ፪፥፲፱–፳፫)።