ኔፊ፣ የኔፊ ልጅ፣ የሔለማን ልጅ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ከሞት በተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ከተመረጡት አስራ ሁለት ደቀመዛሙርቶች መካከል አንዱ (፫ ኔፊ ፩፥፪–፫፤ ፲፱፥፬)። ይህ ነቢይ ለህዝቡ ጥቅም በሀይል ወደ ጌታ ጸለየ። ኔፊ የጌታን ድምፅ ሰማ (፫ ኔፊ ፩፥፲፩–፲፬)። ደግሞም ኔፊ በመላእክት ተጎበኘ፣ ዲያብሎሶችን አስወጣ፣ ወንድሙን ከሞት አስነሳ፣ እናም ለመካድ የማይቻል ምስክር ሰጠ (፫ ኔፊ ፯፥፲፭–፲፱፤ ፲፱፥፬)። ኔፊ የቅዱሣት መጻህፍት መዝገቦችን ጠበቀ (፫ ኔፊ ፩፥፪–፫)።
፫ የኔፊ መፅሐፍ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የኔፊ ልጅ በሆነው ኔፊ የተጻፈ መፅሐፍ። ምዕራፍ ፩–፲ ስለጌታ መምጣት የተተነበዩትን መሟላት ያሳያሉ። የክርስቶስ መወለድ ምልክት ተሰጡ፤ ህዝቡ ንስሀ ገቡ፤ ነገር ግን ወደ ክፋታቸው ተመለሱ። በመጨረሻም አውሎ ንፋስ፤ የምድር መንቀጥቀጥ፣ ሀይለኛ ማዕበል፣ እና ታላቅ ድምሳሴ የክርስቶስን ሞት በምልክት ሰጡ። ምዕራፍ ፲፩–፳፰ ክርስቶስ ወደ አሜሪካ የመጣበትን ይመዘግባሉ። ይህም የ፫ ኔፊ መፅሐፍ ዋና ክፍል ነው። ብዙዎቹ የክርስቶስ ቃላት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሰጣቸው ስብከቶች ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው (ለምሳሌ፣ ማቴ. ፭–፯ እና ፫ ኔፊ ፲፪–፲፬)። ምዕራፍ ፳፱–፴ ለኋለኛው ቀን ሀገሮች ሞርሞን የተናገራቸውቃላትናቸው።
፬ የኔፊ መፅሐፍ
ይህ መፅሐፍ አርባ ዘጠኝ ቁጥሮች ብቻ ነው ያሉት፣ ነገር ግን የኔፋውያን ሶስት መቶ አመት ታሪክን የሚሸፍን ነው። በዚህ መዝገብ የጻፉ ከኔፊ በተጨማሪ ብዙ የጸሀፊ ትውልዶች ነበሩ። ቁጥሮች ፩–፲፱ በትንሳኤ ከተነሳው ጌታ ጉብኝት በኋላ፣ ኔፋውያንና ላማናውያን በሙሉ ወደ ወንጌሉ ተቀየሩ። ሰላም፣ ፍቅር፣ እና ስምምነት ነገሰ። ክርስቶስ እስከ ዳግም ምፅዓቱ ድረስ በምድር እንዲቀሩ የፈቀደላቸው ሶስቱ ኔፋውያን ደቀመዛሙርቱ (፫ ኔፊ ፳፰፥፬–፱) ህዝብን አገለገሉ። ኔፊ መዝገቡን ለልጁ አሞጽ አሳልፎ ሰጠ። ቁጥሮች ፲፱–፵፯ የአሞጽን (፹፬ አመታት) እና የልጁ የአሞጽን (፻፲፪ አመታት) አገልግሎትን መዝግበዋል። በ፪፻፩ ዓ.ም. ውስጥ፣ ትዕቢት እራሳቸውን በመደብ መከፋፈል እና ገንዘብ ለማግኘት የሀሰት ቤተክርስቲያኖችን በጀመሩት ህዝብ መካከል ችግር መፍጠር ጀመረ (፬ ኔፊ ፩፥፳፬–፴፬)።
የ፬ ኔፊ የመጨረሻው ቁጥሮች ህዝቡ እንደገና ወደ ክፋት እንደተመለሱ ያሳያሉ (፬ ኔፊ ፩፥፴፭–፵፱)። በ፫፻፭ ም.ዓ. የአሞፅ ልጅ አሞፅ ሞተ እናም ወንድሙ አማሮን ለጥበቃ ቅዱስ መዝገቦችን ደበቀ። አማሮን በኋላም መዝገቡን የእራሱ የህይወት ጊዜ ብዙ ድርጊቶችን ለመዘገበውና ከእዚያም አሳጥሮ ለጻፋቸው ሞርሞን በእምነት አሳልፎ ሰጠ (ሞር. ፩፥፪–፬)።