ወንጌል ደግሞም ዘመን; የቤዛነት ዕቅድ; የክርስቶስ ትምህርት ተመልከቱ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል እንዲቻል የሆነ የእግዚአብሔር የደህንነት አላማ። ወንጌል ወደ እግዚአብሔር ፊት ለመመለስ የሰው ዘር የሚያስፈልጋቸውን የዘለአለም እውነቶች ወይም ህግጋት፣ ቃል ኪዳኖች፣ እና ስርዓቶች ያጠቃልላል። እግዚአብሔር በ፲፱ኛው መቶ አመት ውስጥ በነቢዩ ጆሴ ስሚዝ በኩል ሙሉ ወንጌልን በምድር ላይ በዳግም መለሰ። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ, ማር. ፲፮፥፲፭. ግልፅና እጅግ የከበረው የበጉ ወንጌል ክፍል ወደ ኋላ ተያዙ, ፩ ኔፊ ፲፫፥፴፪. ይህ ወንጌሌ ነው, ፫ ኔፊ ፳፯፥፲፫–፳፩ (ት. እና ቃ. ፴፱፥፮). መፅሐፈ ሞርሞን ሙሉ ወንጌልን ይዟል, ት. እና ቃ. ፳፥፰–፱ (ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፪). ይህ ወንጌል ነው, ት. እና ቃ. ፸፮፥፵–፵፫. የመልከ ጼዴቅ ክህነት ወንጌሉን ያስተዳድራል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፱. የወንጌል ሙላትን በእራሱ ልሳን እያንዳንዱ ሰው ይሰማል, ት. እና ቃ. ፺፥፲፩. ወልድ ወንጌልን ለሙታን መንፈሶች ሰበከ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፲፰–፳፩፣ ፳፰–፴፯. ወንጌሉ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ መሰበክ ጀመረ, ሙሴ ፭፥፶፰. የወንጌሉ ቀዳሚ መሰረታዊ መርሆችና ስነስርዓቶች ተገልጸዋል, እ.አ. ፩፥፬.