የጥናት እርዳታዎች
ኢዮብ


ኢዮብ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ታላቅ ስቃይ ቢያጋጥመውም በአምላኩ ባለው እምነት ታማኝ የሆነ ጻድቅ ሰው። ታሪኩ በመፅሐፈ ኢዮብ ውስጥ ተነግሯል።

መፅሐፈ ኢዮብ

ምንም እንኳን ይህ መፅሐፍ ስለ ኢዮብ ስቃይ ቢሆንም፣ ለምን ኢዮብ (ወይም ማንኛውም ሌላ ሰው) እንደሚሰቃይ እና ቤተሰቡን ወይም ንብረቱን እንደሚያጣ ሙሉ መልስ አይሰጥም። መፅሐፉም የሚሰቃየው ሰው ኃጢያተኛ ሰው እንዳልሆነም ይገልጻል። ጌታ ስቃይን አጋጣሚ ለመስጠት፣ ለመገሰጽ፣ ለማስተማር እናም ለመቅጣት ይጠቀምበታል (ት. እና ቃ. ፻፳፪)።

መፅሐፉ በአራት ክፍሎች ለመከፋፈል ይችላል። ምዕራፍ ፩–፪ የታሪኩ ማስተዋወቂያ ናቸው። ምዕራፍ ፫–፴፩ በኢዮብ እና በሶስት ጓደኞቹ መካከል ስለነበሩት ንግግሮች ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፴፪–፴፯ የመጀመሪያ ሶስቱ ጓደኞቹ ከወቀሱበት ምክንያት ሌላ ኢዮብን የኮነነው የአራተኛ ጓደኛው የኢሊዮን ንግግሮች የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፴፰–፵፪ መፅሐፉ ኢዮብን የህይወት መንገዱ ከመጀመሪያ ጀምሮ ጥሩ እንደሆነ በማረጋገጥ ይፈፅማል።

መፅሐፈ ኢዮብ ሰው የእግዚአብሔር ትክክል እውቀት ካለው እና በእግዚአብሔር ተቀባይነት ባለው ህይወት ከኖረ፣ በእርሱ ላይ የሚመጡትን ፈተናዎች በመልካም ለመቋቋም እንደሚችል ያስተምራል። የኢዮብ የማይወድቅ እምነት “ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ” በሚለው አባባል ይገለጻል (ኢዮብ ፲፫፥፲፭)። ኢዮብ በሕዝቅኤል ፲፬፥፲፬በየያዕቆብ ፭፥፲፩በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፩፥፲ ውስጥ ተጠቅሷል።