የክብር ደረጃዎች ደግሞም ተረስትሪያል ክብር; ቲለስቲያል ክብር; የሰለስቲያል ክብር ተመልከቱ የሚለያዩ የሰማይ መንግስታት። በመጨረሻው ፍርድ፣ የጥፋት ልጆች ከሆኑት በስተቀር፣ እያንዳንዱ ሰው በልዩ የክብር መንግስት ውስጥ ዘለአለማዊ መኖሪያ ይወርሳሉ። ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ, ዮሐ. ፲፬፥፪ (ኤተር ፲፪፥፴፪). የፀሐይ ክብር አንድ ነው የጨረቃም ክብር ሌላ ነው የከዋክብትም ክብር ሌላ ነው, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፵–፵፩. ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ, ፪ ቆሮ. ፲፪፥፪. ክብር የሌለበትና የዘለአለም ቅጣት የሆነ ቦታ አለ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፴–፴፰፣ ፵፫–፵፭. ሶስት የክብር ክፍሎች አሉ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፻፲፫፤ ፹፰፥፳–፴፪.