ይስሐቅ ደግሞም አብርሐም—የአብርሐም ዘር ተመልከቱ የብሉይ ኪዳን የአባቶች አለቃ። በአብርሐም እና ሣራ በሽምግልናቸው መወለዱ ተአምራት ነበር (ዘፍጥ. ፲፭፥፬–፮፤ ፲፯፥፲፭–፳፩፤ ፳፩፥፩–፰)። አብርሐም ይስሐቅን ለመስዋዕት ማቅረቡ እንደ እግዚአብሔርና እንደ አንድያ ልጁ ምሳሌ ነበር (ያዕቆ. ፬፥፭)። ይስሐቅ ለአብርሐም የተገባው ቃል ኪዳን ወራሽ ነበር (ዘፍጥ. ፳፩፥፱–፲፪፤ ፩ ኔፊ ፲፯፥፵፤ ት. እና ቃ. ፳፯፥፲)። ይስሐቅ ተወለደ, ዘፍጥ. ፳፩፥፩–፯. በሞሪያ ተራራ እንደ መስዋዕት ሊሰዋ ነበር, ዘፍጥ. ፳፪፥፩–፲፱ (ት. እና ቃ. ፻፩፥፬). አገባ, ዘፍጥ. ፳፬. ከልጆቹ ጋር ተነጋገረ, ዘፍጥ. ፳፯፥፩–፳፰፥፱. ከአብርሐምና ከያዕቆብ ጋር ወደ ዘለአለማዊነታቸው ገብቷል, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፴፯ (ማቴ. ፰፥፲፩).