ሩት
በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ እስራኤላውያን ለሆኑት ኑኃሚ እና አቤሜሌክ አማች የነበረች የሞአብ ሴት። ከባሏ ሞት በኋላ፣ ሩት የኒኃሚን ዘመድ ቦዔዝን አገባች። ልጃቸው ኢዮቤድ የዳዊት እና የክርስቶስ ትውልድ ነበር። የሩት ታሪክ እስራኤላዊ ያልሆነችውን ወደ እስራኤል እቅፍ መቀየርን በደንብ ያሳያል። ሩት የድሮ ጣዖቷን እና የድሮ ህይወቷን የእስራኤል እግዚአብሔርን ከሚያገለግል የእምነት ቤት ጋር አንድ ለመሆን ተወች (ሩት ፩፥፲፮)።
መፅሐፈ ሩት
ምዕራፍ ፩ በሞአብ ውስጥ የነበራቸውን የአቤሜሌክ እና የቤተሰቡን ህይወት ይገልጻል። ከባላቸው ሞት በኋላ፣ ኑኃሚ እና ሩት ወደ ቤተልሔም ሄዱ። ምዕራፍ ፪ ሩት ከቦዔዝ ሜዳ ውስጥ እንደ ቃረመች ይገልጻል። ምዕራፍ ፫ ኑኃሚ ሩትን ወደ አውድማ እንድትሄድ እና በቦዔዝ እግር ስር እንድትወድቅ እንዳስተማረቻት ይናገራል። ምዕራፍ ፬ የሩት እና የቦዔዝ ጋብቻ ታሪክ ነው። ኢዮቤድ የሚባል ወንድ ልጅ ወለዱ፣ በእርሱም ትውልድ ዳዊት እና ክርስቶስ ተወለዱ።