ምርጦች ምርጦች እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸው የሚወዱና እርሱን ለማስደሰት ህይወታቸውን የሚኖሩ ናቸው። እንደዚህ አይነት የደቀ መዛሙርት ህይወት የሚኖሩት አንድ ቀን ከተመረጡት ልጆቹ መካከል እንዲሆኑ በጌታ ይመረጣሉ። ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ያታልሏቸውዋል, ማቴ. ፳፬፥፳፬. ዮሐንስ የምርጥ ሴቷ ልጆች እውነትኛ እና ታማኝ ስለሆኑ ተደሰተ, ፪ ዮሐ. ፩. ኃጢያትሽ ተሰርዮልሻል፣ እናም የተመርጥሽ ሴት ነሽ, ት. እና ቃ. ፳፭፥፫. በእኔ የተመረጡት ድምጼን ይሰማሉ እና ልባቸውን አያደንድኑም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፯. ምርጦቼን ከአራቱም የምድር ማዕዘናት ቢሆንም እሰበስባለሁ, ት. እና ቃ. ፴፫፥፮. ቅዱሣት መጻህፍት ለምርጦቼ ደህንነት ይሰጣሉ, ት. እና ቃ. ፴፭፥፳–፳፩. የክህነት ጥሪአቸውን የሚያጎሉ የእግዚአብሔር ምርጥ ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፴፫–፴፬. ለምርጦች የፈተና ቀናት ያጥራሉ, ጆ.ስ.—ማቴ. ፩፥፳.