ነነዌ ደግሞም አሶር; ዮናስ ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የአሶር ዋና ከተማ እና ለሁለት መቶ አመት በታይግረስ ወንዝ በስተምስራቅ ዳር ዋና የንግድ ቦታ ነበር። በ፮፻፮ ም.ዓ. በአሶር ግዛት ውድቀት ጊዜ ወደቀ። የአሶር ንጉስ ሰናክሬ በነነዌ ውስጥ ይኖር ነበር, ፪ ነገሥ. ፲፱፥፴፮. ዮናስ ከተማውን ንስሀ እንዲገቡ ለመጥራት ተላከ, ዮና. ፩፥፩–፪ (ዮና. ፫፥፩–፬). የነነዌ ህዝብ ንስሀ ገቡ, ዮና. ፫፥፭–፲. ኢየሱስ በአይሁዶች ፊት ነነዌን እንደ ንስሀ መግባት ተጠቀመባቸው, ማቴ. ፲፪፥፵፩.