የሮሜ ግዛት
የጥንት ሮሜ ግዛት። በሐዋሪያት ዘመን፣ የሮሜ ግዛት በአለም ውስጥ ታላቅ ሀይል ከነበራቸው አንዷ ነበረች። እርሷም በኤፍራጥስ፣ በዳንዩብ፣ በራይን፣ በአትላንቲክ፣ እና በሰሀራ በረሀ መካከል ያሉትን ሁሉ የያዘች ነበረች። ፖምፒየስ ኢየሩሳሌምን ሲይዝ፣ በ፷፫ ም.ዓ. ፍልስጥኤም ድጋፍ የምትከተል ሀገር ሆነች። ምንም እንኳን ሮሜ አይሁዶችን ብዙ መብቶች ቢሰጧቸውም፣ አይሁዶች የሮሜ ግዛትን ጠሉ እናም በየጊዜውም ያምጹ ነበር።
የሮሜ ዜጋ የነበረው ጳውሎስ፣ በግዛቱ በልምድ የሚጠቀሙበት ቋንቋ የነበረውን የግሪክ ቋንቋ ወንጌልን በግዛት በሙሉ ለማሰራጨት ተጠቀመ።