ኔፊ፣ የሌሂ ልጅ
በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የሌሂና የሳርያ ጻድቅ ልጅ ነው (፩ ኔፊ ፩፥፩–፬፤ ፪፥፭)። ኔፊ በእግዚአብሔር ቃል ታላቅ እምነት ነበረው (፩ ኔፊ ፫፥፯) እና ታላቅ ነቢይ፣ መዝገብ ጠባቂ፣ እና የህዝቡ መሪ ሆነ።
፩ ኔፊ መፅሐፍ
ምዕራፍ ፩ እስከ ፲፰፥፰ በምድረበዳ በሀር ውስጥ ወደ ባህር እስከሚደርሱ ድረስ ተጓዙ። ፩ ኔፊ ፲፰፥፱–፳፫ በጌታ እንደተመሩት፣ ምንም እንኳን ላማን እና ላሙኤል ቢያምጹም ወደ ቃል ኪዳን ምድር ስለተጓዙበት ጉዞ ይናገራሉ። ምዕራፍ ፲፱–፳፪ ኔፊ መዝገቦችን ስለጠበቀበት አላማ ይናገራሉ (፩ ኔፊ ፮፤ ፲፱፥፲፰)፣ ይህም ሁሉም ጌታ ቤዛቸውን እንዲያስታውሱ ለማሳመን ነው። ኢሳይያስን ጠቀሰ (፩ ኔፊ ፳–፳፩) እናም በተስፋ ሁሉም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸውና ቤዛቸው ለማየት እንደሚችሉ የሚገልጸውን የኢሳይያስን ምልእክት ተረጎመ (፩ ኔፊ ፳፪፥፲፪)።
፪ የኔፊ መፅሐፍ
ምዕራፍ ፩–፬ ለልጆቹና ለትውልዶቻቸው ከተሰጣቸው በረከቶች በተጨማሪ፣ ከመሞቱ በፊት የሰጣቸውን የሌሂን የመጨረሻ ትምህርቶች እና ትንቢቶች የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፭ ኔፋያን ከላማናውያን ጋር የተለያዩበትን ምክንያት ይገልጻል። ኔፋውያን ቤተመቅደስ ሰሩ፣ የሙሴ ህግን አስተማሩ፣ እናም መዝገቦችን ጠበቁ። ምዕራፍ ፮–፲ የኔፊ ታናሽ ወንድም የያዕቆብ ቃላትን የያዙ ናቸው። ያዕቆብ የይሁዳን ታሪክ ገመገመ እና ስለመሲህ ተነበየ፣ አንዳንዶቹም ከነቢዩ ኢሳይያስ ፅሁፎች የተወሰዱ ነበሩ። በምዕራፍ ፲፩–፴፫ ውስጥ ኔፊ ስለክርስቶስ ስለነበረው ምስክር፣ ስለያዕቆብ ምስክር፣ ስለኋለኛው ቀናት ትንቢቶች፣ እና ከብሉይ ኪዳን መፅሐፈ ኢሳይያስ ውስጥ አንዳንድ ምዕራፎችን ይመዘግባል።