ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ተመልከቱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ነው (የሐዋ. ፪፥፴፫)። እርሱም በእግዚአብሔር ተቀባይ ከሆነ የሰዎችን ስራዎች፣ ስነስርዓቶች፣ እናም ቃል ኪዳኖች ያረጋግጣል። ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ለአብ የሚያድነው ስነስርዓት በትክክል እንደተከናወነ እና ከእነዚህ ጋር የሚገናኙት ቃል ኪዳናት እንደተጠበቁ ይመሰክራል። በቅዱስ የተስፋ መንፈስ የሚታተሙት አብ ያለውን ሁሉ ይቀበላሉ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶፩–፷ (ኤፌ. ፩፥፲፫–፲፬). ከዚህ ህይወት በኋላ ሀይል እንዲኖራቸው ሁሉም ቃል ኪዳኖች እና ድርጊቶች በቅዱስ የተስፋ መንፈስ መታተም አለባቸው, ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፯፣ ፲፰–፲፱፣ ፳፮.