ታቦት
የጌታ ቤት፣ ከግብፅ በተሰደዱበት ጊዜ እስራኤል የሚያመልኩበት ዋና ቦታ። ታቦቱ ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወር ቤተመቅደስ ነበር እናም መሰባበር እና እንደገና መገንባት ይችል ነበር። የእስራኤል ልጆች የሰለሞን ቤተመቅደስን እስከሚገነቡ ድረስ ታቦትን ተጠቀሙ (ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፴፰)።
እግዚአብሔር የታቦትን ንድፍ ለሙሴ ገለጸ (ዘፀአ. ፳፮–፳፯)፣ እናም የእስራኤል ልጆች በንድፉ መሰረት ገነቡት (ዘፀአ. ፴፭–፵)። ታቦቱ በተፈጸመ ጊዜ ዳመና ድንኳኑን ሸፈነ፣ እናም የጌታ ክብር ታቦቱን ሞላው (ዘፀአ. ፵፥፴፫–፴፬)። ዳመናው የእግዚአብሔር መገኘት ምልክት ነበር። በምሽት፣ የእሳት አመለካከት ነበረው። ዳመናው በድንኳኑ ላይ ሲቀር፣ የእስራኤል ልጆች ይሰፍራሉ። ይህም ተነስቶ ሲሄድ፣ እነርሱም ከእዚህ ጋር አብረው ሄዱ (ዘፀአ. ፵፥፴፮–፴፰፤ ዘኁል. ፱፥፲፯–፲፰)። የእስራኤል ልጆች በበረሀ ውስጥ በሚንቀዋለሉበት ጊዜ እና ቀነዓንን በሚያሸንፉበት ጊዜ ታቦቱን ተሸክመው ይሄዱ ነበር። ጦርነቱን ካሸነፉ በኋላ፣ ጌታ በመረጠበ በሴሎ ታቦቱ ተቀመጠ (ኢያ. ፲፰፥፩)። የእስራኤል ልጆች የሰለሞን ቤተመቅደስን ከገነቡ በኋላ፣ ታቦቱ ከታሪክ በሙሉ ጠፋ።
ጌታ እና ኢሳይያስ ታቦትን በጌታ ዳግም ምፅዓት ጊዜ እንደሚገኙት እንደ ፅዮን ከተማዎች እና ኢየሩሳሌም ምሳሌ ተጠቅመውበት ነበር (ኢሳ. ፴፫፥፳፤ ሙሴ ፯፥፷፪)።