መናዘዝ
ቅዱሣት መጻህፍት መናዘዝን በሁለት መንገዶች ተጠቅመውበታል። በሌላ አባባል፣ መናዘዝ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መናዘዝ አይነት በአንድ ነገር የእራስን እምነት ሁኔታ መግለፅ ነው (ማቴ. ፲፥፴፪፤ ሮሜ ፲፥፱፤ ፩ ዮሐ. ፬፥፩–፫፤ ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፬)።
መናዘዝ፣ እንደ ኃጢያት መናዘዝ አይነት፣ ለራስ ወንጀለኛነት ተቀባይ መሆን ማለት ነው። ሁሉም ሰው ኃጢያቶቻቸውን ሁሉ ለጌታ መናዘዝ እና የእርሱን ምህረት የማግኘት ሀላፊነት አላቸው (ት. እና ቃ. ፶፰፥፵፪–፵፫)። አስፈላጊም ሲሆን፣ ኃጢያቶች ለተሰራበት ወይም ለተሰራባቸው ሰዎች መናዘዝ ያስፈልጋል። ሀይለኛ ኃጢያቶች ለቤተክርስቲያኗ ባለስልጣናት (በብዙም ጊዜ ለኤጲስ ቆጶስ) መናዘዝ ይገባል።