አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ደግሞም ፅዮን ተመልከቱ ቅዱሳን የሚሰበሰቡበት እና ክርስቶስ በአንድ ሺህ አመት ዘመን እራሱ የሚነግስበት ቦታ። ፅዮን (አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ) በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ውስጥ ትመሰረታለች፣ ምድርም ትታደሳለች እናም እንደገነት አይነት ክብር ትቀበላለች (እ.አ. ፩፥፲)። ይህም በአንድ ሺህ ዘመን ጊዜ ከሰማይ የምትወርደውን ቅዱስ ከተማን ይጠቁማል። ከጽዮን ሕግ ይወጣል, ሚክ. ፬፥፪. የጌታ ከተማ ስም አዲሲቱን ኢየሩሳሌም ነው, ራዕ. ፫፥፲፪. ዮሐንስ ቅዱስ ከተማዋን፣ አዲሲቱን ኢየሩሳሌም አየ, ራዕ. ፳፩፥፩–፭. ይህን ህዝብ በዚህች ምድር እመሰርታለሁ፤ እርሷም አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ትሆናለች, ፫ ኔፊ ፳፥፳፪. አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በአሜሪካ ትመሰረታለች, ኤተር ፲፫፥፫–፮፣ ፲. አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከተማ ትዘጋጃለች, ት. እና ቃ. ፵፪፥፱፣ ፴፭፣ ፷፪–፷፱. ቅዱሳን ይሰብሰቡ እናም አዲሲቱ ኢየሩሳሌምን ይመስርቱ, ት. እና ቃ. ፵፭፥፷፫–፸፭. አዲስቱ ኢየሩሳሌም በምዙሪ ተመሰረታለች, ት. እና ቃ. ፹፬፥፩–፭ (ት. እና ቃ. ፶፯፥፩–፫). በጉ በፅዮን ተራራ ላይና በቅዱስ ከተማ፣ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ላይ ይቆማል, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፶፮. ድንኳኔም ፅዮን፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ተብላ ትጠራለች, ሙሴ ፯፥፷፪.