ላባን፣ የነሀስ ሰሌዳዎች ጠባቂ ደግሞም የነሀስ ሰሌዳዎች ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ በሌሂ ቤተሰብ ዘመን ውስጥ በኢየሩሳሌም የነሀስ ሰሌዳዎችን የሚጠብቅ ሰው። ላባን ኔፊንና ወንድሞቹን ዘረፋቸው እናም ሊገድላቸው ሞከረ (፩ ኔፊ ፫፥፩–፳፯)። ሰሌዳዎችን ለማግኘት ኔፊ ላባንን እንዲገድል በመንፈስ ተገፋፋ (፩ ኔፊ ፬፥፩–፳፮)።