መቀደስ፣ የቅድስና ህግ ደግሞም የትብብር ስርዓት; የእግዚአብሔር መንግስት ወይም መንግስተ ሰማያት ተመልከቱ መቀደስ፣ ቅዱስ ማድረግ፣ ወይም ጻድቅ መሆን። የቅድስና ህግ ወንዶች እና ሴቶች ጊዜአቸው፣ ችሎታቸውን፣ እና የንብረት ሀብታቸውን የእግዚአብሔር መንግስትን ለመመስረትና ለመገንባት በምርጫ የሚቀድሱበት መለኮታወ መመሪያ ነው። ዛሬ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ቅዱስ አድርጉ, ዘፀአ. ፴፪፥፳፱. የሚያምኑት ሁሉ ያላቸውንም ሁሉ በአንድነት ያዙ, የሐዋ. ፪፥፵፬–፵፭. ሁሉም ነገሮች በጋራ ነበሩአቸው፣ ስለዚህ ድሃና ሃብታም አልነበራቸውም, ፬ ኔፊ ፩፥፫. ጌታ የቅድስና መሰረታዊ መመሪያን ገለጸ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፴–፴፱ (ት. እና ቃ. ፶፩፥፪–፲፱; ፶፰፥፴፭–፴፮). አንድ ሰው ከሌላ በላይ ንብረት አይኑረው, ት. እና ቃ. ፵፱፥፳. እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ መሰረት በድርሻው እኩል ይሰጠው, ት. እና ቃ. ፶፩፥፫. ቅዱሳን በሰማያዊና በምድራዊ ነገሮች በእኩል እንዲተሳሰሩ ዘንድ ስነስርዓት ተመስርቶ ነበር, ት. እና ቃ. ፸፰፥፬–፭. እያንዳንዱ ሰው በሚፈልገውና በሚያስፈልገው መሰረት እኩል ይገባኛል አለው, ት. እና ቃ. ፹፪፥፲፯–፲፱. ፅዮን በሰለስቲያል ህግ መሰረታዊ መርሆች ብቻ መገንባት ትችላለች, ት. እና ቃ. ፻፭፥፭. ፲፰ የሔኖክ ህዝቦች የአንድ ልብ እና የአንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ እና በጽድቅ ስለኖሩ፣ እና በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም, ሙሴ ፯፥፲፰.