ማፅደቅ፣ ከበደል ነጻ መሆን ደግሞም ቅድስና; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ ተመልከቱ ከቅጣት ምህረት ማግኘት እና ከበደል ነጻ መሆንን ማወጅ። ሰው በኢየሱስም ጸጋ በእርሱ እምነት በኩል ይጻደቃል። ይህም እምነት የሚታየው ንስሀ በመግባት እና ለወንጌሉ ህግጋት እና ስነስርዓቶች ታዛዥ በመሆን ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ የሰው ዘር ንስሀ እንዲገባና ከበደል ነጻ እንዲሆን ወይም ይህ ካልሆነ ከሚቀበሉት ቅጣት ምህረት እንዲያገኙ ያስችላል። የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ, ኢሳ. ፵፭፥፳፭. ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉም, ሮሜ ፪፥፲፫. ሰው በክርስቶስ ደም ጸድቋል, ሮሜ ፭፥፩–፪፣ ፱. እናንተም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጸድቃችኋል, ፩ ቆሮ. ፮፥፲፩. በጸጋው ጸድቀን ወራሾች እንሆናለን, ቲቶ ፫፥፯. አባታችን አብርሃም በሥራ የጸደቀ አልነበረምን, ያዕ. ፪፥፳፩. ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ ጸድቋል, ያዕ. ፪፥፲፬–፳፮. በህግ ማንም ስጋ አይጸድቅም, ፪ ኔፊ ፪፥፭. ጻድቁ ባሪያዬም ብዙዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማልና, ሞዛያ ፲፬፥፲፩ (ኢሳ. ፶፫፥፲፩). ልብሳችሁ በክርስቶስ ደም ጠርቷል ለማለት ትችላላችሁ, አልማ ፭፥፳፯. በጌታችንና አዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የምናገኘው ፅድቅ እውነተኛ ነው, ት. እና ቃ. ፳፥፴–፴፩ (ት. እና ቃ. ፹፰፥፴፱). በመንፈስም ትጸድቃለህ, ሙሴ ፮፥፷.