ሐጌ
በ፭፻፳ ም.ዓ. አካባቢ፣ የአይሁዳ ህዝብ ከባቢሎን ውስጥ ከስደት ወዲያው እንደተመለሱ በኢየሩሳሌም ውስጥ የተነበየ ነቢይ (ዕዝ. ፭፥፩፤ ፮፥፲፬)። የጌታን ቤተመቅደስ በኢየሩሳሌም ውስጥ እንደገና ስለመገንባት ተናገረ እናም ስላልተፈጸመም ህዝብን ገሰጸ። ደግሞም ስለአንድ ሺህ አመቱ ቤተመቅደስ እና ስለ ጌታ ዘመነ መንግስት ጻፈ።
ትንቢተ ሐጌ
በምዕራፍ ፩ ውስጥ፣ ጌታ ህዝብን ቤተመቅደሱ ገና ሳይገነባ እነርሱ ተገንብቶ በተፈጸመ ቤታቸው ውስጥ ስለሚኖሩ ገሰጻቸው። ምዕራፍ ፪ ጌታ በቤተመቅደሱ ውስጥ ሰላም እንደሚሰጥ ሐጌ የተነበየውን ይመዘግባል።