መዘመር ደግሞም መዝሙር; ሙዚቃ ተመልከቱ እግዚአብሔርን በመዝሙር እና በሙዚቃ ግጥም ማምለክ እና ማመስገን። ለጌታ ዘምሩ, ፩ ዜና ፲፮፥፳፫–፴፮ (መዝ. ፺፮). ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ አመስግኑ, መዝ. ፴፥፬. ለእግዚአብሔር እልል በሉ, መዝ. ፻፥፩. መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ, ማቴ. ፳፮፥፴. መንፈስ ቅዱስ እንዲዘምሩ ይመራቸዋል, ሞሮኒ ፮፥፱. የጻድቅን መዝሙር ለእኔ ጸሎት ነው, ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፪. ደስተኛ ከሆናችሁ፣ ጌታን በዘፈን አምልኩ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፰.