የጥናት እርዳታዎች
ኢየሩሳሌም


ኢየሩሳሌም

በእዚህ ዘመን እስራኤል ውስጥ የምትገኝ ከተማ። በታሪካዊ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታላቅ አስፈላጊነት የነበራት ከተማ ናት። ለክርስቲያኖች፣ ለአይሁዶች፣ እና ለእስላሞች ከሁሉም የሚበልጡ አንዳንድ ቅዱስ ቦታዎች በእዚህች ከተማ ውስጥ ይገኛሉ እናም በታማኝ አማኞች በየጊዜው ይጎበኛሉ። ብዙም ጊዜ ቅዱስ ከተማ ተብሎ ይጠራል።

አንድ ጊዜ ሳሌም ተብላ ትታወቅ የነበረችው (ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰መዝ. ፸፮፥፪)፣ ኢየሩሳሌም በዳዊት እስከተያዘች ድረስ የኢያቡሳውያን ከተማ ነበረች (ኢያ. ፲፥፩፲፭፥፰፪ ሳሙ. ፭፥፮–፯)። እስከዚያም ድረስ ከባህር በላይ ፰፻ ሜትር ከፍ ያለች እንደ ተራራ መሸሸጊያ የምትጠቅም ነበረች። ከሰሜን በስተቀር በሁሉም በኩል በጥልቅ ሸለቆዎች የተከበበች ነበረች።

በኢየሩሳሌም ንጉስ ዳዊት በነገሰበት ዘመን፣ የእንጨት ቤተመንግስት ውስጥ ይኖር ነበር። ነገር ግን፣ በሰለሞን ዘመን መንግስት፣ ህዝቡ ከተማዋን ለማስዋብ የንጉስን ቤተመንግስት እና ቤተመቅደስ ከመገንባት በተጨማሪ ብዙ ነገሮች አደረጉ።

የእስራኤል እና የይሁዳ መንግስቶች ከተከፋፈሉ በኋላ፣ ኢየሩሳሌም የይሁዳ ዋና ከተማ ነበረች። በሚወርሩ ሰራዊቶች ብዙ ጊዜ ተጠቅታ ነበር (፩ ነገሥ. ፲፬፥፳፭፪ ነገሥ. ፲፬፥፲፫፲፮፥፭፲፰–፲፱፳፬፥፲፳፭)። በሕዝቅያስ ስር፣ ኢየሩሳሌም የሀይማኖት ማምለኪያ ዋና ቦታ ሆነች ነገር ግን በ፫፻፳ ም.ዓ.፣ በ፻፷፰ ም.ዓ.፣ እና በ፷፭ ም.ዓ. በግማሽ ተደምስሳ ነበር። ሄሮድስ ግድግዳውን እና ቤተመቅደስን እንደገና ገነባ፣ ነገር ግን በ፸ ዓ.ም. በሙሉ ተደመሰሰች።