ፅዮን
ንጹህ ልብ ያለው (ት. እና ቃ. ፺፯፥፳፩)። ፅዮን ደግሞም ንጹህ ልብ ያለው የሚኖርበት ቦታም ማለት ነው። በሔኖክ እና በህዝቡ የተገነባች እና በኋላም ወደሰማይ የተወሰደች ከተማ በጽድቅ ምክንያት ፅዮን ተብላ ተጠርታለች (ት. እና ቃ. ፴፰፥፬፤ ሙሴ ፯፥፲፰–፳፩፣ ፷፱)። በኋለኛው ቀናት ፅዮን የምትባል ከተማ በጃክሰን ግዛት፣ ምዙሪ (ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ) አካባቢ ትገነባለች፣ ወደዚህችም የእስራኤል ጎሳዎች ይሰበሰባሉ (ት. እና ቃ. ፻፫፥፲፩–፳፪፤ ፻፴፫፥፲፰)። ቅዱሳን በአለም በሚኖሩበት በማንኛውም ቦታ ፅዮንን እንዲገነቡ ተበራርተዋል።