እዳ ደግሞም ይቅርታ ማድረግ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ እንደተጠቀሙበት፣ ለሌላ በገንዘብ ወይም በንብረት ባለእዳ መሆን ተበዳሪን በባሪያነት እንደሆነ አይነት ያደርገዋል። በሌላ አመላካከት፣ ኢየሱስ የበደሉንን ይቅር ካልን በኋላ በደላችንን ይቅር እንዲያደርግልን፣ ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል ለኃጢያታችን ክፍያ ከማድረግ እንዲለቀን እንድንጠይቅ አስተምሯል (ማቴ. ፮፥፲፪፤ ፫ ኔፊ ፲፫፥፲፩)። ኃጢአተኛ ይበደራል አይከፍልምም, መዝ. ፴፯፥፳፩. ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው, ምሳ. ፳፪፥፯. ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፣ አንተስ ደግሞ ርህራሄ አይኖርህም, ማቴ. ፲፰፥፳፫–፴፭. እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ, ሮሜ ፲፫፥፰. ለሰማይ አባታችሁ ለዘለአለም እዳ አለባችሁ, ሞዛያ ፪፥፳፩–፳፬፣ ፴፬. ማንም ከጎረቤቱ የተበደረ የተበደረውን ነገር በስምምነቱ መሰረት መመለስ አለበት, ሞዛያ ፬፥፳፰. የገባኸውን እዳ ክፈል፣ እናም ከባርነት ራስህን ነፃ አውጣ, ት. እና ቃ. ፲፱፥፴፭. በጠላታችሁ በኩል እዳ መግባታችሁ የተከለከለ ነው, ት. እና ቃ. ፷፬፥፳፯. እዳችሁን ሁሉ ክፈሉ, ት. እና ቃ. ፻፬፥፸፰. የጌታን ቤት ለመገንባት እዳ አትግቡ, ት. እና ቃ. ፻፲፭፥፲፫.