ሽማግሌው አልማ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በክፉው ንጉስ ኖሀ ቀናት ቤተክርስያኗን ያደራጀ የኔፋውያን ነቢይ። የክፉው ኖሀ ካህን እና የኔፊ ትውልድ ነበር, ሞዛያ ፲፯፥፩–፪. አቢናዲን ካዳመጠ እና ካመነ በኋላ፣ በንጉሱ ተሰደደ። ሸሸ፣ ተደበቀ፣ እና የአበናዲን ቃላት ጻፈ, ሞዛያ ፲፯፥፫–፬. ንስሀ ገባ እና የአበናዲን ቃላት አስተማረ, ሞዛያ ፲፰፥፩. በምርሞን ውሀዎች ውስጥ ጠመቀ, ሞዛያ ፲፰፥፲፪–፲፮. ቤተክርስትያኗን አደራጀ, ሞዛያ ፲፰፥፲፯–፳፱. ከህዝቦቹ ጋር ወደ ዛራሔምላ ደረሰ, ሞዛያ ፳፬፥፳፭. በቤተክርስትያኗ ላይ ስልጣን ተሰጠው, ሞዛያ ፳፮፥፰. ፈረደም ቤተክርስትያኗንም መራ, ሞዛያ ፳፮፥፴፬–፴፱. በልጁ ላይ የሊቀ ካህን ሀላፊነትን አረጋገጠ, አልማ ፬፥፬ (ሞዛያ ፳፱፥፵፪; አልማ ፭፥፫).