ማጎግ
በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ በጥቁር ባህር አካባቢ የሚገኝ ምድርና ህዝብ። ከክርስቶስ ዳግም ምፅዓት በፊት በሚኖረው ታላቅ ጦርነት ንጉሳቸው፣ ጎግ፣ የማጎግ ሰራዊትን ይመራል (ሕዝ. ፴፰፥፪፤ ፴፱፥፮)። በአንድ ሺህ አመት መጨረሻም ላይ በእግዚአብሔር ሀይሎች እና በክፉ ሀይሎች መካከል ስለሚኖረው ስለጎግና ሜጎግ ሌላ ታላቅ ጦርነትም ይናገራሉ (ራዕ. ፳፥፯–፱፤ ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፲፩–፻፲፮)።