ፊት፣ መልክ የመንፈስ አስተሳሰብንና የአዕምሮ ጉዳይን የሚያሳይ፣ የሰው ፊት አጠቃላይ አመለካከት። የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል, ኢሳ. ፫፥፱. የንጉሡ ፊት ተለወጠበት፥ አሳቡም አስቸገረው, ዳን. ፭፥፮. መልኩም እንደ መብረቅ ነበር, ማቴ. ፳፰፥፫. ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሀይ ነበር, ራዕ. ፩፥፲፮. የእግዚአብሔርን ምስል በፊታችሁ ተቀብላችኋልን, አልማ ፭፥፲፬፣ ፲፱. አሞን የንጉሱ ፊት እንደተቀየረ ተመለከት, አልማ ፲፰፥፲፪. በደስተኛ ልብ እና መልክ ጹሙም ጸልዩም, ት. እና ቃ. ፶፱፥፲፬–፲፭. ፊቱም ከሀይል ጸሀይ ብርሀን በላይ የሚበራ ነበር, ት. እና ቃ. ፻፲፥፫.