እሳት ደግሞም መንፈስ ቅዱስ; ምድር—ምድርን ማፅዳት; ሲዖል; ጥምቀት፣ መጥመቅ ተመልከቱ የማፅዳት፣ የማጥራት፣ ወይም የመቅደስ ምልክት። እሳት እንደ እግዚአብሔር በቦታው እንደመገኘቱ ምልክት ሊያገለግል ይችላል። አምላክህ እግዚአብሔር የሚበላ እሳት ነው, ዘዳግ. ፬፥፳፬. መላእክቱን አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል, መዝ. ፻፬፥፬. የሠራዊት ጌታ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል, ኢሳ. ፳፱፥፮ (፪ ኔፊ ፳፯፥፪). ጌታ ከእሳት ጋር ይመጣል, ኢሳ. ፷፮፥፲፭. እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት, ሚል. ፫፥፪ (፫ ኔፊ ፳፬፥፪; ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳፬). እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል, ማቴ. ፫፥፲፩ (ሉቃ. ፫፥፲፮). ፃድቃኖች ከእሳትም እንኳን ቢሆን ይድናሉ, ፩ ኔፊ ፳፪፥፲፯. በደለኞችን በእሳት ይጠፋሉ, ፪ ኔፊ ፴፥፲. ኔፊ እንዴት የእሳት እና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን እንደምንቀበል ገለጸ, ፪ ኔፊ ፴፩፥፲፫–፲፬ (፫ ኔፊ ፱፥፳; ፲፪፥፩; ፲፱፥፲፫; ኤተር ፲፪፥፲፬; ት. እና ቃ. ፴፫፥፲፩). በጥምቀት እናም በእሳት ሃጢያት እንደሚሰረይ አውጅ, ት. እና ቃ. ፲፱፥፴፩. ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን ወደ ሚንቀለቀል እሳት ትጣላለች, ት. እና ቃ. ፳፱፥፳፩. ምድርም በእሳትም እንኳን ቢሆን ትጠፋለች, ት. እና ቃ. ፵፫፥፴፪. የጌታ መገኘትም እሳት እንደሚያቀልጥ ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፵፩. አዳም በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቋል, ሙሴ ፮፥፷፮.