ሪግደን፣ ስድኒ
በ፲፰፻፴ እና በ፲፰፻፵ (እ.አ.አ.) መጀመሪያ መካከል በዳግም በተመለሰችው ቤተክርስቲያን ውስጥ በመጀመሪያ የተቀየረ እና መሪ የነበረ ሰው። ስድኒ ሪግደን ለአንድ ጊዜ በቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር ውስጥ የጆሴፍ ስሚዝ የመጀመሪያ አማካሪ ነበር (ት. እና ቃ. ፴፭፤ ፶፰፥፶፣ ፶፯፤ ፷፫፥፶፭–፶፮፤ ፸፮፥፲፩–፲፪፣ ፲፱–፳፫፤ ፺፥፮፤ ፺፫፥፵፬፤ ፻፥፱–፲፩፤ ፻፳፬፥፻፳፮)። በኋላም ወደቀ እናም በመስከረም ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ተወገዘ።