ማራከስ ደግሞም መስደብ ተመልከቱ ለቅዱስ ነገሮች ክብር አለመኖር ወይም ንቀት። የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ, ዘፀአ. ፳፥፯ (፪ ኔፊ ፳፮፥፴፪; ሞዛያ ፲፫፥፲፭; ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፩). የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለምን እንነቅፋለን, ሚል. ፪፥፲. ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል, ማቴ. ፲፪፥፴፬–፴፯. ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ፣ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም, ያዕ. ፫፥፲. ቃላቶቻችን ይፈርዱብናል, አልማ ፲፪፥፲፬ (ሞዛያ ፬፥፴). ሁሉም ሰዎች እንዴት ስሜን በከንፈሮቻቸው እንደሚይዙ ይጠንቀቁ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፷፩–፷፪.