ጾም፣ መጾም
ወደ ጌታ ለመቅረብና በረከቶቹን ለመጠየቅ ከመብላት ወይም ከመጠጣት በፈቃደኛነት መቆጠብ። ግለሰቦችና ቡድኖች ሲጾሙ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ እና ታላቅ የመንፈስ ጥንካሬ ለማሳደግ ደግመውም መጸለይ ይገባቸዋል። መጾም ሁልጊዜም የእውነተኛ ታማኞች ድርጊት ነበር።
ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ በየወሩ አንድ ሰንበት ቀን ለጾም ተለይቶ የተቀመጠ ነው። በእዚህ ጊዜ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት ለጊዜ ምግብ አይበሉም ውሀም አይጠጡም። ከእዚያም ለእነዚህ ምግቦች ይከፍሉአቸው የነበሩትን ገንዘቦች ለቤተክርስቲያኗ ይሰጣሉ። ይህም ገንዘብ የጾም በኩራት ይባላል። ቤተክርስቲያኗም እነዚህን የጾም በኩራት ደሀዎችንና እርዳታ የሚፈልጉትን ለመርዳት ትጠቀምበታለች።