ሳምራዊ
የሰሜን የእስራኤል መንግስት በአሶር ከተያዘች በኋላ በሰማርያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የመፅሐፍ ቅዱስ ህዝቦች። ሳምራዊዎች በክፍል አይሁዶች እናም በክፍል አህዛብ ነበሩ። ሀይማኖታቸውም የአይሁድ እና የጣዖት አምላኪ እምነትንና ስራን የሚከልስ ነበር። በሉቃ. ፲፥፳፭–፴፯ ውስጥ የሚገኘው የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ ሳምራዊ የእስራኤላውያን ሀይማኖት ስለካዱ አይሁዶች ለሳምራዊን ስላላቸው ጥላቻ ያሳያል። ጌታ ሐዋሪያት ወንጌልን ለሳምራዊ እንዲያስተምሩ መመሪያ ሰጠ (የሐዋ. ፩፥፮–፰)። ፊልጶስ የክርስቶስ ወንጌልን ለሳምራዊ ህዝብ በውጤታማነት ሰበከ እናም በመካከላቸውም ብዙ ታዕምራቶችን አከናወነ (የሐዋ. ፰፥፭–፴፱)።