የጥናት እርዳታዎች
እምነት፣ ማመን


እምነት፣ ማመን

በአንድ ነገር ወይም በአንድ ሰው ላይ ማመን፤ በሰው ላይ ማመን ወይም አንድ ነገርን እንደ እውነት መቀበል። ሰው በእግዚአብሔር መንግስት ለመዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለበት፣ (ት. እና ቃ. ፳፥፳፱)። በቅዱሣት መጻህፍት ላይ በብዙ ጊዜ እንደሚጠቀሙበት፣ እምነት ለእርሱ ታዛዥ ለመሆን የሚመራ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነትን መጣል ነው። ሰውን ወደ ደህናነት ለመምራት እንዲችል እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መመስረት አለበት። ደግሞም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በአብ እግዚአብሔር፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በክህነት ስልጣን ሀይል፣ እና ሌሎች አስፈላጊ በሆኑ በዳግም በተመለሰው ወንጌል አስተያየት ላይ እምነት አላቸው።

እምነት ለማናያቸው፣ ቢሆንም እውነት ለሆኑት ነገሮች ተስፋ መጣልንም ይጠቃልላል (ዕብ. ፲፩፥፩አልማ ፴፪፥፳፩ኤተር ፲፪፥፮)። እምነት የሚነሳሳውም በእግዚአብሔር ስልጣን ተሰጥቷቸው በተላኩ ወንጌሉ ሲያስተምሩ በመስማትም ነው (ሮሜ ፲፥፲፬–፲፯)። ታምራቶች እምነትን አይፈጥሩም፣ ነገር ግን ጠንካራ እምነት የሚያድገው ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ታዛዥ በመሆን ነው። በሌላ አባባልም፣ እምነት የሚመጣው በጽድቅ ነው (አልማ ፴፪፥፵–፵፫ኤተር ፲፪፥፬፣ ፮፣ ፲፪ት. እና ቃ. ፷፫፥፱–፲፪)።

እውነተኛ እምነት ታምራቶችን፣ ራዕዮችን፣ ህልሞችን፣ መፈወስን፣ እና እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሚሰጣቸውን ሁሉ ስጦታዎችን ያመጣል። በእምነት አንድ ሰው የኃጢያት ስርየትን እናም በመጨረሻም በእግዚአብሔር ፊት የመኖር ችሎታን ያገኛል። እምነት ማጣት ሰውን በኃጢያት ምክንያት ወደሚመጣው ተስፋ መቁረጥ ይመራል (ሞሮኒ ፲፥፳፪)።