የጥናት እርዳታዎች
የናስ እባብ


የናስ እባብ

በእግዚአብሔር ትእዛዝ በመርዛማ እባቦች የተነከሱትን እስራኤላውያን ለማዳን ሙሴ የሰራው የናስ እባብ (ዘኁል. ፳፩፥፰–፱)። የናስ እባብ በእንጨት ላይ ተሰቀለ እናም “ቀና ብሎ የተመለከተ እንዲኖር ዘንድ ተሰቀለ” (አልማ ፴፫፥፲፱–፳፪)። ጌታ ስለእባቡ በምድረበዳ ውስጥ መሰቀል በመስቀል ላይ እራሱ እንደተሰቀለበት ምልክት ጠቅሶታል (ዮሐ. ፫፥፲፬–፲፭)። የኋለኛ ቀን ራዕይ የመርዛማው እባብ ታሪክን እና ሰዎች እንዴት እንደዳኑ ያረጋግጣል (፩ ኔፊ ፲፯፥፵፩፪ ኔፊ ፳፭፥፳ሔለ. ፰፥፲፬–፲፭)።