ህያው ውሀ ደግሞም ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስና የትምህርቱ ምልክቶች። ስጋዊ ሰውነትን ለመደገፍ ውሀ አስፈላጊ እንደሆነ፣ አዳኝ እና ትምህርቶቹ (ህያው ውሀ) ለዘለአለም ህይወት አስፈላጊ ናቸው። ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ, ኢሳ. ፲፪፥፫. እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል, ኤር. ፪፥፲፫. እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም, ዮሐ. ፬፥፮–፲፭. ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ, ዮሐ. ፯፥፴፯. የብረት በትር ወደ ህይወት ውሃዎች ምንጭ ይመራል, ፩ ኔፊ ፲፩፥፳፭. ከህይወት ውሃ በነፃ ጠጣ, ት. እና ቃ. ፲፥፷፮. ትእዛዛቴ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፷፫፥፳፫.