ጆሮ ደግሞም ማዳመጥ ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ጆሮ እንደ ሰው የማዳመጥ ወይም የእግዚአብሔር ነገሮችን የማስተዋል ችሎታ ምልክት የሚጠቀሙበት ነው። ጆሮ አላቸው አይሰሙም, መዝ. ፻፲፭፥፮. ጌታ እንድሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል, ኢሳ. ፶፥፬–፭ (፪ ኔፊ ፯፥፬–፭). የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ, ማቴ. ፲፩፥፲፭. ጆሮአቸውም ደንቁሮአል, ማቴ. ፲፫፥፲፭ (ሙሴ ፮፥፳፯). ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው, ፩ ቆሮ. ፪፥፱ (ት. እና ቃ. ፸፮፥፲). ዲያብሎስ በጆሮአቸው አሾከሾከ, ፪ ኔፊ ፳፰፥፳፪. ትሰሙ ዘንድ ጆሮአችሁን ክፈቱ, ሞዛያ ፪፥፱ (፫ ኔፊ ፲፩፥፭). ለብዙ ጊዜ ተጠርቻለሁ፣ እናም አላዳመጥኩም, አልማ ፲፥፮. ቃሌን አድምጥ, አልማ ፴፮፥፩ (አልማ ፴፰፥፩; ት. እና ቃ. ፶፰፥፩). የማይሰማ ጆሮ አይኖርም, ት. እና ቃ. ፩፥፪. ጆሮዎቹ የሚከፈቱት በትሁትነትና በጸሎት በኩል ነው, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፴፪.