ኃጢያተኛ፣ አመፃ ደግሞም ኃጢያት; እድፍ፣ እድፍነት; እግዚአብሔርን የሚጠላ; ክፉ፣ ክፋት; ጻድቅ፣ ጽድቅ ተመልከቱ ክፉ፣ ጻድቅ ያልሆነ፤ እግዚአብሔርን ወይም የእግዚአብሔርን ነገሮች የማይደግፉ እና የእርሱን ምክንያት የማያፈቅሩ ሰዎች። ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም, ፩ ቆሮ. ፮፥፱–፲. በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን ይቀበላሉ, ፪ ተሰ. ፪፥፲፪. ኢየሱስ ክርስቶስ ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን ይችላል, ፩ ዮሐ. ፩፥፱. ፃድቅ ያልሆነ ንጉስ የፃድቃንን መንገድ በሙሉ እንደዚህ ያጣምማል, ሞዛያ ፳፱፥፳፫. የዚህ ህዝብ ጥፋት መሰረቱ ፃድቃን ባልሆኑት ጠበቆቻችሁና ዳኞቻችሁ መጣል ጀምሯል, አልማ ፲፥፳፯. ጻድቅ ላልሆነው ስራዎቻቸው ዓለምን እንዲወቅሱ ልኬአችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፹፯. ነፍስ ጻድቃን ካልሆኑት ሁሉ መንጻት አለባት, ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፯–፲፰. በቶሎ ጻድቅ ባልሆነ ሁኔታ ስልጣናቸውን እንደሚጠቀሙበት፣ የምንም ያህል ሰዎች ሁሉ ፍጥረት እና ባህሪይ ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፱.