መጥላት፣ ጥላቻ ደግሞም በቀል; ጠላትነት; ፍቅር ተመልከቱ ጥላቻ አንድን ሰው ወይም ነገር አለመውደድ ነው። እኔ እግዚአብሔር በሚጠሉኝ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣው, ዘፀአ. ፳፥፭. እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው, ምሳ. ፮፥፲፮. ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ይንቃል, ምሳ. ፲፭፥፳. የተናቀ ከሰውም የተጠላ ነው, ኢሳ. ፶፫፥፫. ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ, ማቴ. ፭፥፵፬. ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል, ማቴ. ፮፥፳፬. በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ, ማቴ. ፲፥፳፪. ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል, ዮሐ. ፫፥፳. ማንም ታናሽነትህን አይናቀው, ፩ ጢሞ. ፬፥፲፪. ሀብታም በመሆናቸው ድሆችን ይጠላሉ, ፪ ኔፊ ፱፥፴. የእግዚአብሔርን ራዕይ አትናቁ, ያዕቆ. ፬፥፰. ከእኛ ዘለዓለማዊ የሆነ ጥላቻ ነበራቸው, ያዕቆ. ፯፥፳፬. ሰዎች የእግዚአብሔርን ምክር ከንቱ ያደርጋሉ እናም ቃሉንም ይንቃሉ, ት. እና ቃ. ፫፥፯. ራዕይ አይቻለሁ በማለቴ ተጠላሁ እናም ተሰቃየሁ, ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፳፭.