ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት ደግሞም ማመንዘር; ምኞት; በወሲብ የስነ ምግባር ጉድለት; ንጹህነት; ዝሙት መፈጸም ተመልከቱ ሳድቅ ላልሆነ የሰውነት ደስታን፣ በልዩም የወሲብ የስነ ምግባር ጉድለትን፣ ማፍቀር ወይም መውደድ። የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች, ዘፍጥ. ፴፱፥፯. ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል, ማቴ. ፭፥፳፰ (፫ ኔፊ ፲፪፥፳፰). ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ራቁ, ፩ ጴጥ. ፪፥፲፩. የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ከአባት አይደሉም, ፩ ዮሐ. ፪፥፲፮. በዓይንህ ምኞት ከእንግዲህ እንዳትጓዝ, አልማ ፴፱፥፱. ቅዱስ ህጎችን በመተላለፍ ሰዎች ስጋዊ ሆኑ, ት. እና ቃ. ፳፥፳. ማንም በልባቸው ካመነዘሩ፣ መንፈስም አይኖራቸውም, ት. እና ቃ. ፷፫፥፲፮. ከፍተኛ ፍላጎታችሁን ሁሉ አቁሙ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፩. ሰዎችም ስጋዊ፣ ስሜታዊና ዲያብሎሳዊ መሆን ጀመሩ, ሙሴ ፭፥፲፫ (ሞዛያ ፲፮፥፫; ሙሴ ፮፥፵፱).