ኬብሮን ከኢየሩሳሌም በሰላሳ ሁለት ኪሎ ሜትር ወደ ደቡብ አልፎ የሚገኝ የጥንት የይሁዳ ከተማ። የአብርሐም እና የቤተሰቡ መቃብር ቦታ ነበር (ዘፍጥ. ፵፱፥፳፱–፴፪)። በዳዊት የመጀመሪያ ዘመነ መንግስት ዋና ከተማውም ነበረ (፪ ሳሙ. ፭፥፫–፭)።