የክርስቶስ ልጆች ደግሞም መወለድ; ኢየሱስ ክርስቶስ; የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች; ዳግመኛ መወለድን፣ ከእግዚአብሔር መወለድ ተመልከቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን የተቀበሉት። እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው, ማቴ. ፲፰፥፩–፬. የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ በብርሃኑ እመኑ, ዮሐ. ፲፪፥፴፮. ፍጥረታዊው ሰውነትን ቀይር እናም እንደ ልጅ ሁን, ሞዛያ ፫፥፲፱፤ ፳፯፥፳፭–፳፮. በገባችሁት ቃል ኪዳን የተነሳ የክርስቶስ ልጆች ትባላላችሁ, ሞዛያ ፭፥፯. መልካም የሆኑትን ሁሉ የምትይዙ ከሆነ፣ እናም ካልኮነናችሁት፣ በእርግጥ እናንተ የክርስቶስ ልጆች ትሆናላችሁ, ሞሮኒ ፯፥፲፱. ለተቀበሉኝ ሁሉ ልጆቼ እንዲሆኑ ኃይልን ሰጠኋቸው, ት. እና ቃ. ፴፱፥፬. አትፍሩ፣ ህጻናት፣ የእኔ ናችሁና, ት. እና ቃ. ፶፥፵–፵፩. አንተ በእኔ አንድ ነህ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ, ሙሴ ፮፥፷፰.