ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፪


ክፍል ፻፳፪

በመጋቢት ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) በልብርቲ እስር ቤት፣ ሚዙሪ ውስጥ ታስሮ እያለ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የመጣ የጌታ ቃል። ይህ ክፍል በመጋቢት ፳፣ ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ለቤተክርስቲያኗ ከተጻፈ ደብዳቤ ውስጥ የተወሰደ ነው (ክፍል ፻፳፩ ርዕስን ተመልከቱ)።

፩–፬፣ የምድር ዳር ሁሉ ስለጆሴፍ ስሚዝ ስም ይጠይቃሉ፤ ፭–፯፣ እርሱ ያጋጠሙት የአደጋ ሁኔታዎች እና ስቃዮች ልምድን ይሰጡታል እና ለእርሱም ጥቅም ይሆናሉ፤ ፰–፱፣ የሰው ልጅ ከሁሉም በታች ወርዷል።

የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ስለስምህ ይጠይቃሉ፣ እና ሞኞችም በአንተ ይሣለቁብሀል፣ እና ገሀነምም በአንተ ላይ ይቆጣል፤

ንጹህ ልብ ያለው እና ጥበበኛው፣ እና ልኡሉ፣ እና ምግባረ መልካሙ ከእጆችህ ምክርን፣ እና ስልጣንን፣ እና በረከትን ዘወትር ይሻል።

እና ህዝብህም በከዳተኛ ምስክር ምክንያት ከአንተ ላይ ድጋፋቸውን አይቀይሩም።

እና ምንም እንኳን የእነርሱ ተጽዕኖ ወደ ችግርና ወደ አጥሮች እና ግድግዳዎች ቢጥልህም፣ ትከብራለህ፤ እና ይህም ለጥቂት ጊዜ እና በፅድቅህም ምክንያት ድምፅህም በጠላቶችህ መካከል ከአደገኛ አምበሳ በላይ የሚያስፈራ ይሆናል፤ እናም አምላክህም በአጠገብህ ለዘለአለም ይቆማል።

በፈተናዎች እንድታልፍ ከተጠራህ፤ በሀሰተኛ ወንድሞች መካከል በአደጋ ሁኔታዎች ውስጥ ካለህ፤ በዘራፊዎች መካከል በአደጋ ሁኔታዎች ውስጥም ብትሆን፤ በምድር ወይም በባህር በአደጋ ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆን፤

በሀሰት ክሶች ብትከሰስ፤ ጠላቶችህም ቢያጠቁህ፤ ከአባትህና እናትህ እና ከወንድሞችህና እህቶችህ ህብረት ነጥለው ቢወሰዱህ፤ እና በተመዘዘ ጎራዴ ጠላቶችህ ከሚስትህ እቅፍ እና የስድስት አመት እድሜ ያለው ልጅህም፣ ልብስህንም አጥብቆ በመያዝ፣ አባዬ አባዬ ለምን ከእኛ ጋር ለመቆየት አትችልም? አባዬ ሆይ፣ ሰዎቹ ምን ሊያደርጉብህ ነው? ብሎ ከሚል ከታላቅ ልጅህ ነጥለው ቢወስዱህ፤ እና ከዚያም እርሱ ከአንተ በጎራዴ ተገፍቶ፣ እና አንተም ወደ እስር ቤት ብትጎተት፣ እና ጠላቶችህም በዙሪያህ ለጥቦው ደም እንደሚያንዣብቡ ተኩላ ቢሆኑም፤

እና ወደ ጉድጓድ ወይም በገዳዮች እጅም ብትጣል፣ እና የሞት ፍርድ ቢተላለፍብህ፤ ወደ ጥልቁም ብትጣል፤ ወደፊት እና ወደኋላ የሚገፋው ውሀ በአንተ ላይ ቢያድም፤ አደገኛው ነፋሶስም ጠላትህ ቢሆን፤ ሰማያትም ጭለማን ቢሰበስቡ፣ እና ንጥረ-ነገሮች ሁሉ መንገድህን ለማሰናከል ቢጣመሩ፤ እና ከሁሉም በላይ፣ የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊው ብትከፍትብህ፣ ልጄ ሆይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ።

የሰው ልጅ ከሁሉም በታች ወርዷል። አንተ ከእርሱ ታላቅ ነህ?

ስለዚህ፣ ባለህበት መንገድ ቆይ፣ እና ክህነትም ከአንተ ጋር ይቆያልገደቦቻቸው ተወስነዋል፣ ሊያልፉትም አይችሉም። ቀናትህ የታወቁ ናቸው እና አመታትህም ከዚህ በታች አይቀነሱም፤ ስለዚህ፣ ሰው ማድረግ የሚችለውን አትፍራ፣ እግዚአብሔር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ከአንተ ጋር ነውና።