ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፲፪


ክፍል ፲፪

ግንቦት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለጆሴፍ ናይት ቀዳማዊ፣ የተሰጠ ራዕይ። የመፅሐፈ ሞርሞንን ሰሌዳ መያዙን እና በሂደት ላይ ያለውን የትርጉም ስራ በተመለከተ ጆሴፍ ስሚዝ የሰጠውን መግለጫ ጆሴፍ ናይት አመነ እናም መተርጎም እንዲቀጥሉ ያስቻላቸውን የቁሳቁስ እርዳታ፣ ለጸሐፊው እና ለጆሴፍ ስሚዝ ብዙ ጊዜ ሰጥቶ ነበር። በጆሴፍ ናይት ጥያቄ፣ ጆሴፍ ስሚዝ ጌታን በመጠየቅ ራእዩን ተቀብሏል።

፩–፮፣ በወይኑ ስፍራ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነትን ያገኛሉ፤ ፯–፱፣ የሚሹ እና ብቁ የሆኑ ሁሉ በጌታ ስራ ውስጥ መርዳት ይችላሉ።

በሰዎች ልጆች መካከል ታላቅ እና ድንቅ ስራ ሊመጣ ነው።

እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ፈጣን እና ሀያል፣ ሁለት አንደበት ካለው ሰይፍ ይልቅ የተሳለ፣ መገጣጠሚያን እና መቅኔን የሚለየውን ቃሌን አድምጥ፤ ስለዚህ ቃሎቼን እድምጥ።

እነሆ፣ የእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ አዝመራው ዝግጁ ነው፣ ስለዚህ፣ ለነፍሱ ዘለአለማዊ ደህንነትን በእግዚአብሔር መንግስት ያከማች ዘንድ፣ መሰብሰብ የሚሻ በኃይሉ ይጨድ፣ እናም ቀን ሆኑም እያለ ይሰብስብ።

ማንኛውም የሚያጭድ እናም የሚሰበስብ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተጠራ ነው።

ስለዚህ፣ ብትጠይቀኝ ትቀበላለህ፣ ብታንኳኳ ይከፈትልሀል።

አሁን፣ እንደጠየከው፣ እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ ትዛዛቴን ጠብቅ እናም የፅዮንን እንቅስቃሴ ለመፈጸም እና ለመመስረት ፈልግ፤

እነሆ፣ ለአንተ እና እንዲሁም ይህንን ስራ ለመፈጸምና ለመመስረት ለሚሹ ሁሉ እናገራለሁ።

በሀላፊነት እምነት በተጣሉበት ነገሮች ሁሉ ራሱን ገዝቶ፣ በእምነትበተስፋና በለጋስነት፣ እናም እራሱን ትሁት በማድረግና በፍቅር ተሞልቶ ካልሆነ በቀር፣ ማንም ሰው በዚህ ስራ ውስጥ መርዳት አይችልም።

እነሆ፣ እነዚህን ቃላት የምናገረው እኔ የአለም ብርሀን እና ህይወት ነኝ፣ ስለዚህ ባለህ ሀይል አድምጥ እናም ከዚያም ትጠራለህ። አሜን።