ክፍል ፱
ሚያዚያ ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። ኦሊቨር ትዕግስተኛ እንዲሆን ተገሰጸ እናም ለመተርጎም ከመሞከር ይልቅ ለጊዜው የተርጓሚውን ቃላት በመጻፍ እንዲደሰት ተመከረ።
፩–፮፣ ሌሎች ጥንታዊ መዛግብት ገና ይተርጎማሉ፤ ፯–፲፬፣ መፅሐፈ ሞርሞን በጥናት እና በመንፈሳዊ ማረጋገጫ ተተረጎመ።
፩ እነሆ፣ ልጄ ሆይ እንዲህ እልሀለሁ፣ ከእኔ በፈለከው መሰረት ስላልተረጎምህ እናም ዳግም ለአገልጋዬ፣ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ መጻፍን በመጀመርህ ምክንያት በእርሱ ላይ እምነት የጣልኩበትን መዝገብ እስክትጨርስ ድረስ እንድትቀጥል እፈልጋለሁ።
፪ እና ከዚያም እነሆ፣ ሌሎች መዛግብቶች አሉኝ፣ ያንንም በመተርጎም እንድትረዳ ኃይል እሰጥኃለሁ።
፫ ልጄ ትዕግስተኛ ሁን፣ ይህ በእኔ ዘንድ ጥበብ ነውና፣ እናም በአሁኑ ጊዜ መተርጎምህ አስፈላጊ አይደለም።
፬ እነሆ፣ እንድታደርገው የተጠራህበት ስራ ለአገልጋዬ ለጆሴፍ እንድትጽፍ ነው።
፭ እናም፣ እነሆ፣ ይህንም እድል ከአንተ የወሰድኩብህ መተርጎም በጀመርህ ጊዜ እንደ ጀመርኸው ባለመቀጠልህ ምክንያት ነው።
፮ አታጉረምርም፣ ልጄ ሆይ፣ ከአንተ ጋር በዚህ ሁኔታ ይህን ማድርጌ ጥበብ ነው።
፯ እነሆ፣ አልተረዳህም፤ እኔን ከመጠይቅህ በስተቀር ምንም ሳታስብበት፣ እንደምሰጥህ ገምተህ ነበር።
፰ ነገር ግን እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ በአእምሮህ ውስጥ ልታጠናው ይገባል፤ ከዚያም ትክክለኛ መሆኑን ልትጠይቀኝ ይገባል፣ እናም ትክክለኛ ከሆነ ውስጥህም እንዲቃጠል አደርጋለሁ፤ ትክክል እንደሆነም ይሰማሀል።
፱ ነገር ግን ትክክል ካልሆነ እንደዚህ ያሉ ስሜቶች አይሰሙህም፣ ነገር ግን የተሳሳተ ነገርን የሚያስረሳ የሀሳብ ብዥታ ይሆንልሀል፤ ስለዚህ፣ ከእኔ ካልተሰጠ በስተቀር ቅዱስ የሆነውን መጻፍ አትችልም።
፲ አሁን፣ ይህን አውቀህ ቢሆን ኖሮ መተርጎም በቻልህ ነበር፤ ሆኖም፣ አሁን መተርጎምህ አስፈላጊ አይደለም።
፲፩ እነሆ፣ በጀመርህበት ጊዜ አስፈላጊ ነበር፤ ነገር ግን ፈራህ፣ እናም ጊዜውም አለፈ፣ እናም አሁን አስፈላጊ አይደለም፤
፲፪ የጠፋውን ጊዜ ለመተካት ለአገልጋዬ ጆሴፍ በቂ ጥንካሬን አብጅቼ እንደሰጠሁት አታይምን? እናም ማናችሁንም ቢሆን አልኮነንኩም።
፲፫ እንድታደርግ ያዘዝኩህን አድርግ፣ እናም ትበለጽጋለህ። ታማኝ ሁን፣ እናም ለፈተና ራስህን አታጋልጥ።
፲፬ አንተን ለጠራሁበት ስራ ጸንተህ ቁም፣ እናም ከራስ ጠጉርህ አንዲት አትጠፋም፣ እናም በመጨረሻውም ቀን ከፍ ትላለህ። አሜን።