ክፍል ፷፭
ጥቅምት ፴፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ስለጸሎት የተሰጠ ራዕይ።
፩–፪፣ የእግዚአብሔር የመንግስቱ ቁልፎች በምድር ለሰው ተሰጥተዋል፣ እናም ወንጌሉም አሸናፊ ይሆናል፤ ፫–፮፣ የአንድ ሺህ ዘመን መንግስተ ሰማያት ይመጣል እናም በምድርም በእግዚአብሔር መንግስት ጋር ተዋሀዳለች።
፩ አድምጡ፣ እናም ሀያል እና ጠንካራ የሆነው፣ አካሄዱም እስከ ምድር ዳርቻ የሆነውን፣ አዎን ድምጹም ለሰዎች የሆነውን፣ ከላይም እንደተላከ ድምጽ የሆነውን፣ እነሆ—የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውንም አቅኑ፤
፪ በምድርም ለሰው የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎችም ተሰጥተዋል፣ እናም ከዚህም ወንጌሉ፣ እጅም ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ፣ ወደ ምድር ዳርቻምይገፋል።
፫ አዎን፣ ድምፅም ይጮሀል—የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ የበጉን እራት አዘጋጁ፣ ለሙሽራውም ተዘጋጁ።
፬ ወደ ጌታም ጸልዩ፣ ቅዱስ ስሙንም ጥሩ፣ በአህዛብም መካከል ድንቅ ስራዎቹን እንዲታወቁ አድርጉ።
፭ የዚህች ኗሪዎችም እንዲቀበሉት፣ መንግስቱም በምድር ላይ እንዲሄድ፣ ጌታን ጥሩ፣ እናም የሰው ልጅ የክብሩን ብርሀን ለብሶ ከሰማይ በምድር ከተሰራችው የእግዚአብሔርን መንግስት ጋር ለመገኛኘት በሚገለጥበት ወደ ፊት ለሚመጡት ቀናትም ተዘጋጁ።
፮ ስለዚህ፣ መንግስተ ሰማያት እንድትመጣ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ወደ ፊት ይሂድ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰማይም እንዳከበርህ እንዲሁ በምድርም ትከበር ዘንድ፣ ጠላቶችህም ይዋረዱ ዘንድ፤ ክብርም፣ ኃይልም፣ እና ግርማም የአንተ ናትና፣ ከዘለአለም እስከዘለዓለም። አሜን።