ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፸፬


ክፍል ፸፬

በ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.)፣ በዌይን አውራጃ፣ ኒው ዮርክ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ቤተክርስቲያኗ ከመደራጀቷ በፊትም፣ ነቢዮ ስለ ርዕሱ መልስ እንዲፈልግ ያደረጉ ስለትክክለኛው የጥምቀት መንገድ ጥያቄዎች ነበሩ። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ ይህ ራዕይ የህጻናት ጥምቀት ተቀባይነትን ለማሳየት ሁልጊዜም የሚጠቀሙበትን የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰት፣ ፩ ቆሮንቶስ ፯፥፲፬ን የሚያብራራ ነው።

፩–፭፣ ጳውሎስ በጊዜው የነበረችውን ቤተክርስቲያን የሙሴን ህግጋትን እንዳታከብር መከረ፤ ፮–፯፣ ህጻናት ልጆች ቅዱስ ናቸው እናም በኃጢአት ክፍያውም የተቀደሱ ናቸው።

ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሶአልና፥ ያላመነችም ሚስት በባልዋ ተቀድሳለች፤ አለዚያ ልጆቻችሁ ርኵሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።

አሁን፣ በሐዋርያት ዘመን የግርዘት ህግ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በማያምኑት አይሁዶች ዘንድ ይተገበር ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ በህዝብም መካከል የግርዘት ህግን የሚመለከት ታላቅ ክርክር ተነስቶ ነበር፣ ያላመነ ባል ልጆቹ እንዲገረዙ እና ተፈጽሞ ለነበረውም ለሙሴ ህግ ተገዢ እንዲሆን ፍላጎት ነበረውና።

እናም እንዲህም ሆነ፣ ልጆቹም በሙሴ ህግ ተገዢ ሆነው በማደጋቸው፣ የአባቶቻቸውን ባህሎች ተከተሉ እናም በክርስቶስም ወንጌል አላመኑም፣ በዚህም ያልተቀደሱ ሆኑ።

ስለዚህ፣ በዚህም ምክንያት ነው ሐዋሪያው ለቤተክርስቲያኗ ከጌታ ሳይሆን ከራሱ፣ በመካከላቸው የሙሴ ህግ ካልተሻረ በስተቀር የሚያምኑ ከማያምኑ ጋር አንድነት የላቸውምበማለት የጻፈው፣

ልጆቻቸው እንዳይገረዙ፤ እና ይህም በአይሁዶች መካከል ይተገበር ስለነበር፣ ህጻናት ልጆች አይጸደቁም የሚለው ባህልም እንዲቀር የትእዛዝን ፅሑፍ ሰጣቸው፤

ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአት ክፍያ አማካይነት ስለተቀደሱ ህጻናት ልጆች የተቀደሱ ናቸው፤ እና ይህም የቅዱሳት መጻህፍት ትርጉም ነው።