ክፍል ፻፲፩
በነሀሴ ፮፣ ፲፰፻፴፮ (እ.አ.አ.) በሴለም ማሳቹሰት ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ጊዜ በአገልግሎት ስራዎቻቸው ምክንያት የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ብዙ እዳ ነበረባቸው። በሴለም ውስጥ ብዙ ገንዘቦች እንደሚገኝላቸው በመስማት፣ ነቢዩ፣ ስድኒ ሪግደን፣ ሀይረም ስሚዝ፣ እና ኦሊቨር ካውድሪ ወንጌልን ከመስበክ ጋር የተባለውን ለመመርመር ከከርትላንድ ኦሀዮ ወደ እዚያ ተጓዙ። ወንድሞች የቤተክርስቲያኗን ብዙ ጉዳዮች አከናወኑ እና ጥቂትም ሰበኩ። ምንም ገንዘብ እንደማይገኝ ግልፅ እየሆነ ሲመጣም፣ ወደ ከርትላንድ ተመለሱ። በስረ መሰረታቸው በግልፅ የሚታዩት ብዙዎቹ ጉዳዮች በዚህ ራዕይ ቃላት ውስጥ ተገንዝበዋል።
፩–፭፣ ጌታ የአገልጋዮቹን ስጋዊ ፍላጎቶች ይጠብቃል፤ ፮–፲፩፣ ፅዮንን በምህረት ይንከባከባታል እና ለአገልጋዮቹም መልካነትም ሁሉንም ነገሮች ያዘጋጃል።
፩ ስሀተተኞች ብትሆኑም፣ እኔ ጌታ አምላካችሁ በዚህ ጉዞ በመምጣታችሁ ያልተደሰትኩባችሁ አይደለሁም።
፪ በዚህ ከተማ ለእናንተ፣ ለፅዮን ጥቅም፣ ብዙ ሀብቶች አሉኝ፣ እና በዚህ ከተማም በእናንተ መሳሪያነት ለፅዮን ጥቅም በጊዜዬ ሰብስቤ የማወጣቸው ብዙ ህዝብም አሉ።
፫ ስለዚህ፣ እንደምትመሩት፣ እና እንደሚሰጣችሁ፣ ከዚህ ከተማ ሰዎች ጋር ባልንጀሮች መሆናችሁ በእኔ ዘንድ አስፈላጊ ነው።
፬ እና በጊዜውም፣ በዚህ ከተማ ላይ ሀይል ይኖራችሁ ዘንድ፣ በዚህም የሚስጥር ክፍላችሁን እንዳያገኙባችሁ ዘንድ ይህን ከተማ በእጆቻችሁ አሳልፌ የምሰጥበት ጊዜ ይመጣል፤ እና ስለወርቅ እና ስለብር በሚመለከትም ሀብትም የእናንተ ይሆናል።
፭ ስለእዳዎቻችሁ አታስቡ፣ እንድትከፍሏቸውም ሀይልን እሰጣችኋለሁና።
፮ ስለፅዮንም አታስቡ፣ እርሷንም በምህረት እንከባከባታለሁና።
፯ በዚህ ስፍራ እና በአካባቢዋ ክፍለ ሀገሮች ቆዩ፤
፰ እና እናንት በብዛት እንድትቆዩበት ፍቃዴ በሚሆንበት ስፍራም በውስጣችሁ የሚፈልቀው መንፈሴ ሰላምና ሀይል ምልክት ይሰጣችኋል።
፱ ይህንም ስፍራ በኪራይ አግኙት። ስለዚህ ከተማ የጥንት ነዋሪዎችና መስራቾችን በቅንነት ጠይቁ፤
፲ በዚህ ከተማ ውስጥ ከአንድ በላይ ሀብቶች አሉአችሁና።
፲፩ ስለዚህ፣ ያለኃጢአት እንደ እባብ ብልህ ሁኑ፤ እና እናንት ልትቀበሉ በምትችሉት ፍጥነትም፣ ሁሉንም ነገሮች ለእናንተ መልካምነት አዝዛለሁ። አሜን።