አስተዳደሪያዊ አዋጅ ፪
መፅሐፈ ሞርሞን እንደሚገልጸው፣ “ሁሉም ለእግዚአብሔር አንድ ናቸው፣” እንዲሁም “ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውና ነፃው፤ ሴትና ወንድ” (፪ ኔፊ ፳፮፥፴፫)። በቤተክርስቲያኗ ታሪክ በሙሉ፣ የእያንዳንዱ ዘረ አባል የሆኑ የብዙ ሀገሮች ሰዎች ተጠምቀዋል እናም እንደ ቤተክርስቲያኗ ታማኝ አባላት ኖረዋል። በጆሴፍ ስሚዝ ህይወት ውስጥ፣ አንዳንድ ጥቁር ወንድ አባላት በክህነት ተሾመው ነበር። በታሪኳ መጀመሪያ፣ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ከአፍሪካ ትውልድ ለሆኑ ወንድ አባላት ክህነትን መስጠት አቆሙ። የቤተክርስቲያኗ መዝገቦች የዚህ ልምድን መጀመሪያ ምን እንደሆነ ምንም አስተያየት አይሰጡም። የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ይህን ልምድ ለመቀየር የእግዚአብሔር ራዕይ አስፈላጊ መሆኑን አምነው ነበር እናም በጸሎት መመሪያን ፈለጉ። ራዕይም ለፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል መጣ እናም በሰኔ ፩፣ ፲፱፻፸፰ (እ.አ.አ.) ለሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ይህም ተረጋግጦ ነበር። ራዕዩም በክህነት ላይ በዘር ምክንያት የሚገድበውን በሙሉ እንዲወገድ አደረገ።
ለሚመለከተው ሁሉ፥
በመስከረም ፴፣ ፲፱፻፸፰ (እ.አ.አ.)፣ በ፻፵፰ኛው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአመቱ ግማሽ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ በቤተክርስቲያኗ ቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ ፕሬዘደንት ኤን ኤልደን ታነር የሚቀጥለው ቀረበ፥
በዚህ አመት ሰኔ መጀመሪያ ላይ፣ ክህነትን እና የቤተመቅደስ በረከቶችን ለሁሉም ብቁ የቤተክርስቲያን አባላት ሁሉ ስለመስጠት ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል ራዕይ ተቀብለው እንደነበር ቀዳሚ አመራር አስታወቁ። በቅዱስ ቤተመቅደስ በተቀደሰ ክፍሎች ውስጥ ከረጅም ጥልቅ ሀሳብ እና ጸሎት በኋላ የመጡላቸውን ይህን ራዕይ ከተቀበሉ በኋላ፣ ይህን ለተቀበሉት እና ለተስማሙት አማካሪዎቻቸው እንዳቀረቡ ለጉባኤው እንድነግር ፕሬዘደንት ኪምባል ጠይቀውኝ ነበር። ከዚያም ይህ ለአስራ ሑለቱ ሐዋርያት ቡድን ቀረበ፣ እነርሱም በአንድ ድምፅ ተስማሙበት፣ እና በኋላም ለሁሉም አጠቃላይ ባለስልጣናት ቀረበ፣ እነርሱም በተመሳሳይ ሁኔታ በአንድ ድምፅ ተስማሙበት።
ፕሬዘደንት ኪምባል አሁን ይህን ደብዳቤ እንዳነብ ጠይቀውኛል፥
ሰኔ ፰ ቀን ፲፺፻፸፰
በአለም አቀፍ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ እና የአካባቢ የክህነት ሀላፊዎች ሁሉ፥
ውድ ወንድሞች፥
የጌታ ስራ በምድር ላይ ሲያድግ በምስክርነቱን ስናይ፣ የብዙ ሀገሮች ህዝብ ዳግም የተመለሰውን የወንጌል መልእክት ስለተቀበሉ፣ እና ዘወትር በሚያድግ ቁጥሮች በቤተክርስቲያኗ አባል ስለሆኑ ምስጋና አለን። ይህም በተራው ወንጌሉ የሚያቀርባቸውን ሁሉንም መብቶች እና በረከቶች ለእያንዳንዱ ብቁ የቤተክርስቲያን አባላት ለማቅረብ ያለንን ፍላጎት አነሳስቶናል።
አንድ ቀን በእግዚአብሔር ዘለአለማዊ አላማ ብቁ የሆኑት ወንድሞቻችን ሁሉ ክህነትን እንደሚቀበሉ ከእኛ በፊት የነበሩት የቤተክርስቲያኗ ነቢያት እና ፕሬዘደንቶች የሰጡትን የተስፋ ቃል እያወቅን፣ እና ከክህነት ስልጣን ተወግደው የነበሩትን ታማኝነት ምስክር በመሆን፣ ብዙ ሰዓቶችን በቤተመቅደሱ ታላቅ አዳራሽ ውስጥ ጌታን ለመለኮታዊ አመራር በመለመን ለረጅም ጊዜ እና በቅንነት ለእነዚህ ታማኝ ወንድሞቻችን ለምነን ነበር።
ጸሎታችንን ሰምቷል፣ እና በራዕይም እያንዳንዱ ታማኝ፣ ብቁ ወንድ ሰው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ መለኮታዊ ስልጣኑን ለመጠቀም ካለው ሀይል ጋር፣ ቅዱስ ክህነትን ለመቀበል እና ከቤተመቅደስ በረከት በተጨማሪ፣ ከሚወዳቸው ጋር ከዚያ የሚፈሱትን እያንዳንዱን በረከት እንዲደሰቱ ለረጅም ጊዜ ቃል የተገባለት ቀንም እንደደረሰ አረጋግጧል። በዚህም መሰረት፣ የቤተክርስቲያኗ ብቁ ወንድ አባላት ለዘር ወይም ቀለም ትኩረት ሳይሰጥ ወደክህነት ስልጣን ሊሾሙ ይችላሉ። የክህነት መሪዎችም ለዚህ ለአሮናዊ ወይም ለመልከ ጼዴቅ ክህነት ሹመት ተመራጭ ለሆኑት ሁሉ ለብቁነት የተመሰረተውን መሰረቶች እንደሚያሟሉ ለማረጋገጥ የጥንቃቄ ቃል ጥያቄ አመራርን እንዲከተሉ ታዝዘዋል።
ጌታ በአለም ውስጥ ሁሉ ያሉትን የባለስልጣን አገልጋዮቹን ድምፅ የሚያዳምጡትን እና የወንጌል እያንዳንዱ በረከቶችን ለመቀበል ራሳቸውን የሚያዘጋጁ ልጆቹን ለመባረክ ያለውን ፍላጎት እንዳስታወቀ በትጋት እናውጃለን።
በቅንነት የእናንተው፣
ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል
ኤን ኤልደን ታነር
ሜሪዮን ጂ ሮምኒ
ቀዳሚ አመራር
ስፔንሰር ደብሊው ኪምባልን እንደ ነቢይ፣ ገላጭ፣ እና ባለራዕይ፣ እና እንደኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት በመቀበል፣ እኛ እንደ አባል ተሰብሳቢዎች ይህን ራዕይ እንደ ጌታ ቃል እና ፈቃድ እንድንቀበል ቀርቦልናል። ይህን የሚቀበሉ ቀኝ እጃቸውን በማንሳት ያሳዩ። የሚቃወሙም በዚህ አይነት ምልክት።
ይህ የቀረበው ሀሳብ በአንድ ድምፅ ምርጫ በአዎንታዊነት ተደግፏል።
ሶልት ሌክ ስቲ፣ ዩታ፣ መስከረም ፴ ቀን ፲፱፻፸፰ (እ.አ.አ.)።