ክፍል ፴፪
ጥቅምት ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) መጀመሪያ አካባቢ በማንቸስተር፣ ኒው ዮርክ ውስጥ በጆሴፍ ስሚዝ አማካይነት ለፓርሊ ፒ ፕራት እና ለዚባ ፒተርሰን የተሰጠ ራዕይ። ቤተክርስቲያኗ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ በረከታቸው ቀደም ብሎ እንደተተነበየላቸው ሰለተገነዘበቻቸው ላማናውያን በተመለከተ በሽማግሌዎች መካከል ታላቅ ፈቃድ እና አትኩሮት አድሮ ነበር። በዚህ የተነሳ ጌታ በምራዕብ ወዳሉት የኢንድያን ጎሳዎች ሽማግሌዎች እንዲሄዱ ፈቃዱ እንደሆነ ለመጠየቅ ታላቅ ጸሎት ተደረገ። ይህ ራዕይም ተከተለ።
፩–፫፣ ፓርሊ ፒ ፕራት እና ዚባ ፒተርሰን ከኦሊቨር ካውድሪ እና ፒተር ዊትመር ዳግማዊ ጋር በመሆን ለላማናውያን እንዲሰብኩ ተጠሩ፤ ፬–፭፣ ቅዱሳን መጻህፍትን ለመረዳት መጸለይ አለባቸው።
፩ እናም አሁን አገልጋዬን ፓርሊ ፒ ፕራትን በተመለከተ፣ እነሆ፣ እንዲህ እለዋለሁ፣ እኔ ህያው እንደሆንኩኝ፣ ወንጌሌን እንዲያውጅ እናም ከእኔም እንዲማር እንዲሁም የዋህ እና ልበ ትሁት እንዲሆን ፍቃዴ ነው።
፪ እናም እኔ ለእርሱ የሰጠሁት ከአገልጋዮቼ፣ ከኦሊቨር ካውድሪ እና ከፒተር ዊትመር ዳግማዊ፣ ጋር በላማናውያን መካከል ወደ ምድረበዳ እንዲሄድ ነው።
፫ እናም ዚባ ፒተርሰን እንዲሁ ከእነርሱ ጋር ይሄዳል፤ እኔም ራሴ ከእነርሱ ጋር እሄዳለሁ፣ እናም በመካከላቸውም እሆናለሁ፤ እናም ከአብ ዘንድ እኔ የእነርሱ አማላጅ ነኝ፣ እናም ምንም ነገር እነርሱን አይቃወምም።
፬ እናም ለተጻፉት ትኩረትን ይሰጣሉ፣ እናም ሌላን ራዕይ ተቀበልን አይሉም፤ እናም እነዚህን ነገሮች እንዲገባቸው ግልጽ አደርግላቸው ዘወትር ይጸልያሉ።
፭ እናም ለእነዚህ ቃላት ያድምጣሉ እና በቀላሉም አይመለከቷቸውም፣ እናም እባርካቸዋለሁ። አሜን።